Sunday, 20 April 2014

የሦስት ምድብ አራት አመት ወቅቶች እና የጳጉሜ 6 እለት ሰዓት ስርጭታዊ አፈጣጠር

6.6.4. የሦስት ምድብ አራት አመት ወቅቶች እና የጳጉሜ 6 እለት ሰዓት ስርጭታዊ አፈጣጠር "ጳጉሜ 6 "የቀን መቁጠሪያው የማን ነው? " የሚል ርእስ ተጠቅሟል፡፡ የኛም ጥያቄ ነው፡፡ ያን ያህል የተለፋበት የቀን መቁጠሪያ የማን ነው? የኢትዮጵያንን ቀን መቁጠሪያ እንደማይመለከት በግልጽና በቀጥታ ስንናገር ግን በሀዘን ብቻ ሳይሆን በቁጭትም ጭምር ነው፡፡ ግን ግን ለምንድነው ይሄ ቀን መቁጠሪያ እንዲህ በምሑራኑ ሳይቀር በሚገባ ላይታወቅ የቻለው? ስለርሱ ከተጻፉት ውስጥ አንዳችም ስህተት የሌላቸው ስንቶቹ ይሆኑ?"በሚል በአቶ ሰለሞን አበበ ቸኮል የቀረበው ጥያቄ ጳጉሜ 6ን ፈጹም ካለማወቅ የመነጨ ነው፡፡ የሦስት ምድብ አራት አመት ወቅቶች እና የጳጉሜ 6 እለት ሰዓት ስርጭታዊ አፈጣጠር ሰንጠረዥ ማለት በእጅ ሰዓት እና በቀን መቁጠሪያ ላይ በአራት አመት አንዴ ብቻ የምተመዘገበው ጳጉሜ 6 እለት በየምድብ አመት እያነዳነዱ ወቅት ክረምት፤ መፀው በጋ እና ፀደይ እና በየወቅቱ እያነዳነዱ ምድብ አመት ተደምሮ ተመሳሳይ 24 ሰዓት በመስጠቱን የሚያሳይ የጊዜ ሰንጠረዥ ነው፡፡ የሰንጠረዡ ረድፍ በየምድብ አመቱ እያነዳነዱ 4 ተከታታ ወቅት ውስጥ የተጠራቀመ የጳጉሜ 6 እለት ሰዓት ድርሻ እና ድምራቸውን ሲያሳይ፤ የሰንጠረዡ አምድ እያነዳነዱ ወቅት በየምድብ አመቱ የተጠራቀመ የጳጉሜ 6 ሰዓት ድርሻ እና ድምራቸውን ያሳያል፡፡ ሰንጠረዡ እንዴት ይነበባል? በመጀመሪያ የሰንጠረዡ ረድፍ እና በሁለተኛ ደረጃ የሰንጠረዡ አምድ በመመልከት የጳጉሜ 6 ሰዓት ድርሻ ይነበባል፡፡ ለምሳሌ በምድብ አመት ሀ (1) ረድፍ አንድ ላይ 1.545206 ሰዓት ተጽፋል፤ ከዚያ ወደ አምድ አንድ ስናነብ ክረምት (1) የሚል ቃል እናገኛለን፡፡ ስለዚህ በ1ኛው ረድፍ እና በ1ኛው አምድ ስር የተመለከተው 1.545206 ሰዓት ማለት በምድብ አነድ አመት በ1ኛው ክረምት ወቅት የተጠራቀመ የጳጉሜ 6 ሰዓት ብዛት 1.545206 ነው፡፡ በተመሳሳይ የማንበብ ዘዴ በ1ኛው ረድፍና 2ኛ አምድ ስር 1.463014 የመፀው፤ 3ኛ አምድ ስር 1.479452 የበጋ ፤4ኛ አምድ ስር 1.512329 የፀደይ እና ድምራቸው በ5ኛ አምድ ስር 6 ሰዓት መሆኑን እናያለን፡፡ በመሆኑም በምድብ አንድ አመት የተጠራቀመ የጳጉሜ 6 እለት ድረሻ 6 ሰዓት ነው፡፡ በምድብ ሁለት አመት ሁለተኛ እረድፍ (2) እና በ1ኛው አምድ ስር 3.090412 የክረምት፤2ኛው አምድ ስር 2.926027 የፀደይ ፤3ኛው አምድ ስር 2.958903 የበጋ ፤4ኛው አምድ ስር 3.024658 የፀደይና ድምራቸው በ5ኛው አምድ ስር 12 ሰዓት መሆኑን ያሳያል፡፡ ምድብ ሁለት አመት ማለት ሁለት ተከታታይ መደበኛ አመቶች ስለሆኑ የተጠራቀመ የጳጉሜ 6 ሰዓት ብዛት 12 ሰዓት ነው፡፡ በምድብ ሦሥት አመት፤ ሦሥተኛ እረድፍ (3) እና በ1ኛው አምድ ስር 1.545206 የክረምት፤2ኛው አምድ ስር 1.463014 የፀደይ ፤3ኛው አምድ ስር 1.479452 የበጋ ፤4ኛው አምድ ስር 1.512329 የፀደይንና ድምራቸው በ5ኛው አምድ ስር 6 ሰዓት መሆኑን ያሳያል፡፡ በመጨረሻ የሰዓት ድምር በአራተኛው ረድፍ (4) እና በ1ኛው አምድ ስር 6.180822 የክረምት፤2ኛው አምድ ስር 5.852055 የመፀው ፤3ኛው አምድ ስር 5.917808 የበጋ ፤4ኛው አምድ ስር 6.049315 የፀደይንና ድምራቸው በ5ኛው አምድ ስር 24 ሰዓት የሆነው ከላይ በየምድብ አመቱ ከተጠራቀመው 24 ሰዓት ( 6+12+6) ጋር እኩል ነው፡፡