… በየዓመቱ በተጠጋጋ ተረፍ የሆነዉ 6 ሰዓት በ4ዓመት ተጠራቅሞ 24 ሰዓት ወይም አንድ ዕለት አስገኝቶ ጳጉሜን በ4ዓመት አንዴ 6 እንደሚያደርጋት ሁሉ የ6 ካልዒት ትርፍ በዕርግጥ ካለ( የአለ ግን አይመስለኝም) በ600 ዓመት አንዴ ጳጉሜ 7 ትሆናለች፡፡ ̋
ከላይ በጥቅስ የተመለከተዉ ድምዳሜ በዘመናዊ ማስረጃ እና መረጃ ትንተና ዘዴ ባለመታገዙ ምክነንያት የሚከተሉት ተግዳሮቶች አሉበት፡፡ (1ኛ) ጳጉሜ 6 የ7 ተግባራዊ ተያያዥ የጊዜ መለኪያ አሃዶች ምንጭ መሆኑን እና ከእያንዳንዱ 1461 አሃዶች ዉስጥ የመጨረሻዉ አሃድ (marginal unit) ጳጉሜ 6 መሆኑን አላወቀም፡፡ (2ኛ) ከእያንዳንዱ ሰባት የጊዜ አሀዶች ውስጥ የማይመዘገበው ጳጉሜ 6 ምን ያህል የጊዜ አሃድ እየሆነ ነው? ለሚለዉ ጥያቄ መልስ አልሰጠም፡፡ (3ኛ) ጳጉሜ 6 ከሰብቴምበር 11 አንፃር ሲፈተሸ ሁለት አዲስ የጊዜ ንድፈ ሃሰቦችን ማስገኘቱ አልታወቀም፡፡ (4ኛ) የጳጉሜ 6 ሳምንት እለት እና ዓመተ ምህረት ከሰብቴምበር 11 ሳምንት እለት እና ዓመተ ምህረት ፍፁም የተለየ መሆኑ አልታወቀም፡፡ በመሆኑም ጳጉሜ 6 እና ሰብቴምበር 11 የሚመዘገቡበት የሳምንት እለት ስም እና የእምርታ አመተ ምህረት የታወቁ፤ እየታወቁ ያሉ እና ወደፊትም መታወቃቸዉ ከግንዛቤ አልገባም፡፡
ሰባት ተግባራዊ የጊዜ መለኪያ አሃዶች
ሰባት የተያያዙ የጊዜ መለኪያ አሃዶች በስራላይ ይገኛሉ፡፡ አሃድ ማለት በቁጥር የተለየ መስፈሪያ ማለት ነዉ፡፡ ከታች የተመለከተዉ ሰንጠረዥ 1፡1 ሰባት የተያያዙ የጊዜ መስፈሪያ አሃዶች ከሚመዘገቡበት አሰራር መሳሪያ አንፃር በሦሥት ትናንሽ (ሰከንድ፤ ደቂቃ፤ ሰዓት) እና በአራት ትላልቅ (እለት፤ ሳምንት፤ ወር እና አመት) የተከፈሉ መሆናቸዉን ያሳያል፡፡ በመሆኑም 1 ሰከንድ ማለት ከ60 ሰከንዶች ዉሥጥ አንዱ ማለት ነዉ፡፡ 1 ደቂቃ ማለት የ60 ሰከንዶች መስፈሪያ ማለት ነዉ፡፡ 1 ሰዓት ማለት የ60 ደቂቃ ስፍር ወይም 1 ደቂቃ 60 ጊዜ በመደጋገም የተጠራቀመ ጊዜ ማለት ነዉ፡፡ 1 እለት ማለት በ24 ሰዓት የተሰፈረ ጊዜ ማለት ነዉ፡፡ 1 ሳምንት ማለት በ7 እለት የተሰፈረ ጊዜ ማለት ነዉ፡፡ 1 ወር ማለት በ4 ሳምንት ከ 2 እለት፤ 5 ሳምንት እና 5 ሳምንት ከ 1 እለት የተሰፈረ ጊዜ ማለት ነዉ፡፡ 1 ዓመት ማለት በ12 ወሮች ወይም በ52 ሳምንት ከ1 እለት ወይም ከ2 እለት ወይም በ365 እለት በአራት አመት አንዴ 366 እለት የተሰፈረ ጊዜ ማለት ነዉ፡፡
ከላይ በሰንጠረዥ 1፡1 የተመለከቱት 7 የተያያዙ የጊዜ መለኪያ አሃዶች በመጠናቸዉና ከሚመዘገቡበት የአሰራር መሳሪያ አንፃር በሁለት ተከፍለዉ ይገኛሉ፡፡ የመጀመሪያዎቹ 3 ተከታታይ ትናንሽ የጊዜ መለኪያ አሃዶች ሰከንድ፤ ደቂቃ እና ሰዓት በእጅ ሰዓት ወይም በግድግዳ ሰዓት ይመዘገባሉ፡፡ በመሆኑም ከጥዋት ፀሃይ ፍንጥቅ ካለችበት እስትጠልቅ ድረስ ያለዉን 12 ሰዓት ቀን ከ 1 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ከቀትር በፊት እና ከ6 ሰዓት ማብቂያ እስከ 12ሰዓት ከቀትር በሁዋለ መሆኑን፤ እንዲሁም ፀሃይ ከጠለቀችበት አስከንጋት ድረስ ያለዉን 12 ሰዓት ለሊት ከቀኑ 12 ሰዓት ማብቂያ እስከ ለሊቱ 6 ሰዓት ግማሽ ለሊት እና ከ6 ሰዓት ማብቂያ እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ከእኩለ ለሊት በሁዋላ መሆኑን በትክክል የምንቆጣጠረዉ በእጅ ሰዓት ነዉ፡፡ በእጅ ሰዓት የተመዘገበዉ 12 ሰዓት ቀን እና 12 ሰዓት ለሊት አንድላይ 24 ሰዓት በመሆን አንድ እለት የተሰኘዉን አሃድ ይሰጠናል፡፡
ነገር ግን የእጅ ሰዓት እለትን መመዝገብ አይችልም፡፡ በመሆኑም ሁለተኛዉ 4 ተከታታይ ትላልቅ የጊዜ መለኪያ አሃዶች እለት፤ ሳምንት፤ ወር እና ዓመት የሚመዘገቡት የአሳራር መሳሪያ ቀን መቁጠሪያ ይባላል፡፡
የእለት ፅንሰ ሃሳብ መሰረት የምድር አንድ ሹረት ነው፡፡ ለአብነት ፀሃይ ከሰሜን ሰፊ ሞቃት ጫፍ ተመልሳ በምድር ወገብ የዋለችበትን እለት ወስደን ብንመለከት የሰሜንና ደቡብ ሰፊ ሞቃት ምድረ ሰማይ ወር እለት ሥም መስከረም 13 ከሰሜንና ደቡብ ጠባብ ቀዝቃዛ ምድረ ሰማይ ወር እለት ሰብቴምበር 23 በፍፁም የተለየ መሆኑን ምስል 1.2 ያሳያል፡፡ ሥለዚህ መስከረም 13 ማለት የሞቃት ምድር 24 ሰዓት እኩል በ12 ሰዓት ቀን እና በ12 ሰአት ለሊት መከፈሉን ሲያመለክት፤ ሰብቴምበር 23 ማለት ግን የቀዝቃዛ ምድር 24 ሰዓት እኩል በ12 ሰዓት ቀን እና በ12 ሰአት ለሊት መከፈሉን ያሳያል ፡፡ በመሆኑም ለãሃይ የተጋለጠው ግማሽ የምድር ክፍል 12 ሰዓት ቀን ሲባል ከፀሃይ የተሰወረው ግማሹ ምድር 12 ሰዓት ለሊት ይባላል (ምስል 1.2 የመልከቱ)፡፡
ከእለት ቀጥሎ በቀን መቁጠሪያ ላይ የሚመዘገበዉ በጣም ትልቁ የጊዜ መለኪያ አሃድ ምንድን ነዉ? በጣም ትልቁ የጊዜ መለኪያ አሃድ 7 እለት ይዞ የሚገኘዉ ሳምንት ነዉ፡፡ የአንድ ሳምንት አሃድ 7 ነዉ ማለት አንድ እለት 7 ጊዜ በመደጋገም የሚገኝ የእለት ብዛት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ የሳምነት እለት ብዛት 7 የሆነዉ ለምንድን ነዉ? ለሚለዉ ጥያቄ የተገኘዉ መልስ በጳጉሜ 6 እለት ምንጭነት ነዉ፡፡ በየአመቱ 6 ሰዓት ከእጅ ሰዓትና ከቀን መቁጠሪያ ሳይመዘገብ እየተረፈ በየ4 ዓመት 1461ኛ እለት ላይ በመከሰት የሚመዘገበው ጳጉሜ 6፤ ከእለት ቀጥሎ ከሚገኘዉ ትልቅ የጊዜ መለኪያ አሃድ ጋር እኩል በመሆን 1461ኛ ሁኖ የሚመዘገበው መቼ ነው? የሚል ጥያቄ ሲነሳ የተገኘው መልስ በየ 28 ዓመት ከ 7 እለት ጋር ነው፡፡ በመሆኑም በ28 አመታት ውስጥ ካሉት 1461 ሳምንቶች ውስጥ የመጨረሻው 7 እለት የጳጉሜ 6 ሳምነት ነው፡፡ በመሆኑም የአንድ ሳምንት እለት ብዛት 7 ብቻ የመሆን ብያኔ ምንጭ የጳጉሜ 6 እለት መሆኑ የሚያሳየን የፀሃይና የሰፊ ሞቃት ምድር ጊዜ ፍፁም ሳይነሳዊ መሆኑን ነዉ፡፡
ከሳምንት ቀጥሎ በቀን መቁጠሪያ ላይ የሚመዘገበዉ እጅግ በጣም ትልቁ የጊዜ መለኪያ አሃድ ምንድን ነዉ? ከሳምንት ቀጥሎ የሚገኘዉ እጅግ በጣም ትልቁ ጊዜ ወር ነው፡፡ ወር የሚይዘው የጊዜ ብዛት 4 ሳምንት ከ 2 እለት ነው፡፡ ነሐሴና ጳጉሜ እንደ አንድ ወር በሚወሰዱብት ጊዜ አንድ ወር ማለት 5 ሳምንት ይሆናል፡፡ በአራት አመት አነዴ ይህው ልዩ ወር 5 ሳምንት ከአንድ እለት ይሆናል፡፡ ወር ለሚባለው የጊዜ መለኪያ አሃድ ስም ምንጭ ምንድን ነው? ወር ለሚለው ጽንሰ ሃሳብ መሰረት ጨረቃ ሙሉ እየሆነች የምትታይበት ጊዜ ብዛት ነው፡፡ ጨረቃ ሙሉ እየሆነች የምትወለደው በየ29.5 እለት ነው፡፡ በመሆኑም የወር መስፈሪያ አሃድ 30 እለት ተደረገ ማለት ነው፡፡ በአመት ውስጥ የሚገኙት የወር ብዘት 12 ብቻ መሆን ብያኔ መሰረት ምንድን ነው? የሚለውን ጥያቄ ከመመለሳችን በፊት ከወር መስፊያ ቀጥሎ ጊዜ የተሰፈረው አመት በተሰኘ ፅንሰ ሃሳብ መሆኑን እንመለከታለን፡፡
ከወር የሚቀጥለው ትልቁ የጊዜ መለኪያ ምንድን ነዉ? አመት ነው፡፡ የአመት ጽንሰ ሃሳብ መሰረት ምድር በየ24 ሰዓት በሰፊዉ ሞቃት ክፍል እየፈጠነች እና በጠባቡ ቀዝቃዛ ክፍል እየተንቀረፈፈች በመሾር ãሃይን አንዴ ዙራ ለመጨረስ የሚወስድባት ጊዜ 365.25 እለት ነው፡፡ በመሆኑም ዘመናዊዉ የአመት ጊዜ መለኪያ አሃድ 365 እለት ለተከታታይ ሶስት አመት እና በየ አራት ዓመት 366 እለት ነው፡፡ የአመት እለት ብዛት አሃድ ብያኔ ምንጭ እንዲሁ የጳጉሜ 6 እለት ነው፡፡ በመቀጠል የፀሃይ አመት 365 እና 366 እለት በስንት 30 እለት መደብ መከፈል አለበት የሚለው ጥያቄ ሲነሳ የተገኘው መልስ 12 መደብ እና ቀሪ 5 እና ባራት አመት አንዴ 6 እለት ነው፡፡ ስለዚህ የፀሃይ ዓመት በ12 ወሮች መደብ የተሰፈረ ነው ፡፡ እንዲሁም ከእየሱስ ክርስቶስ መወለድ ጀምሮ አመት በቁጥር የሚመዘገበዉ ዓመተ ምህረት የሚል ስያሜ ይዞ ነዉ፡፡
በመሆኑም አመት የአመተ ምህረት ቁጥር፤ 12 ወሮች፤ በ12 ወሮች ውስጥ 52 ሳምንታትና 1 እለት እና በአራት አመት አንዴ 2 እለት የያዘ ትልቁ የጊዜ መለኪያ ነው፡፡ በመሆኑም ከሰዓት ቀጥለው የሚገኙት 4 ተከታታይ የጊዜ መለኪያ አሃዶች እለት፤ሳምንት፤ወር እና አመት የሚመዘገቡት እጅግ በጣም የረቀቀ መሳሪያ የቀን መቁጠሪያ ይባላል፡፡
በአጠቃላይ ሰንጠረዥ 1.1 እያንዳነዱ ትንሽ የጊዜ አሀድ መጠን ለተከታዩ አሀድ መጠን መሰረት መሆኑን ያሳያል፡፡ ማለትም ሰከንድ ለደቂቃ፤ደቂቃ ለሰዓት፤ሰዓት ለእለት፤እለት ለሳምንት፤ሳምንት ለወር እና ወር ለዓመት መሰረትና ተያያዥ ናቸው፡፡ ከላይ ከተ.ቁ 1 እስከ 3 የተመለከቱትን የጊዜ አሃዶች በእጅ ሰዓት ይመዘገባሉ፡፡ ከተ.ቁ 4 እስከ 7 የተመለከቱት የጊዜ አሃዶች የሚመዘገቡት በቀን መቁጠሪያ ላይ ነው፡፡
ከእያንዳነዱ 7 ዘመናዊ የጊዜ አሀዶች የማይመዘገበው ጳጉሜ 6
ከእያንዳንዱ ሰባት የጊዜ አሀዶች ውስጥ የማይመዘገበው ጳጉሜ 6 ምን ያህል የጊዜ አሃድ እየሆነ ነው? ለሚለዉ ጥያቄ መልስ ቢሰጡ ኖሮ የጊዜ ተፈጥሮ ማስረጃ እና መረጃ የሌለዉን የዉሸት ጳጉሜ 7 አያስተጋቡም ነበር፡፡ ነገር ግን ሰንጠረዥ 1.2 ከእያንዳንዱ የጊዜ አሀዶች ውስጥ የማይመዘገበው ጳጉሜ 6 ምን ያህል የጊዜ አሃድ እየሆነ ነው? የሚለውን ጥያቄ በዝርዝር መልስ ይሰጣል፡፡ ከእያንዳነዱ ሰከንድ በእጅ ሰዓት ሳይመዘገቡ የሚቀሩት የጳጉሜ 6 ማይክሮ ሰከንዶች 0.000684462968 ናቸዉ፡፡ እነኝህ በየሰከንዱ ያልተመዘገቡት የጳጉሜ 6 ማይክሮ ሰከንዶች ተጠራቅምው በየደቂቃው 0.041067761 ሰከንዶች ይሞላሉ፡፡ በየደቂቃዉ የማይመዘገቡት የጳጉሜ 6 ሰከንዶች ተጠራቅመዉ በየሰአቱ 2.464065708 ሰከንዶች ይሆናሉ፡፡ በየሰአቱ የማይመዘገቡት የጳጉሜ 6 ሰከንዶች ተጠራቅምው በየእለቱ ከ 59 ሰከንዶች በላይ እና ከአንድ ደቂቃ በታች ይሞላሉ፡፡ በየእለቱ የማይመዘገቡት የጳጉሜ 6 ሰከንዶች ተጠራቅመዉ በየሳምንቱ 413.963039 ሰከንዶች ወይም ከ 6 ደቂቃ በላይ ይሞላሉ፡፡በየሳምንቱ የማይመዘገቡት የጳጉሜ 6 ሰከንዶች ወይም ደቂቃዎች ተጠራቅመዉ በየወሩ 1800 ሰከንዶች ወይመወ 30 ደቂቃ ይሞላሉ፡፡ በመጨረሻ በየወሩ ያልተመዘገቡት የጳጉሜ 6 ሰላሳ ደቂቃዎች ተጠራቅመዉ በየአመቱ 21600 ሰከንዶች ወይም 360 ደቂቃዎች ወይም 6 ሰዓት ይሞላሉ ማለት ነዉ፡፡
በየአመቱ ያለተመዘገቡዉ የጳጉሜ 6 ስድስት ሰዓት ተጠራቅሞ በየአራት አመት አንዴ 24 ሰዓት ወይም አንድ እለት ይሞላል፡፡ በመሆኑም የጊዜያችን ቀመር ምንጭ የሆነችውን ጳጉሜ 6 ስንመለከት ጳጉሜ 6 በእጅ ሰዓት እና በቀን መቁጠሪያው የምትመዘገበው በአራት አመት አንዴ በየ 1461 ኛው እለት ላይ (1461=365.25*4) ነው፡፡ ስለዚህ ጳጉሜ 6 በአራት አመት የታሰረች በመሆኑ የተነሳ ከዚያ የሚተርፍ ጊዜ የለም፡፡ ስለዚህ የአቶ አብነት ስሜ ጳጉሜ 7 መረጃና ማስረጃ የሌለዉ ዉሸት ነዉ፡፡
ጳጉሜ 6 ከሰብቴምበር 11 አንፃር
ጳጉሜ 6 ከሰብቴምበር 11 አንፃር ማለት በሁለት አዲስ የተፈጥሮ ጊዜ ንድፈ ሃሳቦች መሰረት እጅግ በጣም ረቅቀዉ የተሰሩ የአሰራር መሳሪያዎች መሆናቸዉን የሚያሳይ ነዉ፡፡ ሁለቱ የጊዜ ንድፈ ሃሳቦች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡ንድፈ ሃሳብ አንድ፡-የሰሜንና ደቡብ ሰፊ ሞቃት ምድር ፈጣን ሹረትና ዙረት ማለት አጭር የቀንና ለሊት ሰዓት ልዩነትና አራት መካከለኛ ተቃራኒ ወቅቶች መከሰታቸውን የሚመለከት ነዉ፡፡ ንድፈ ሃሳብ ሁለት፡-የሰሜንና ደቡብ ጠባብ ቀዝቃዛ ምድር ቀርፋፋ ሹረትና ዙረት ማለት እጅግ ረጅም የቀንና ለሊት ሰዓት ልዩነትና አራት ከፍተኛ ተቃራኒ ወቅቶች መከሰታቸውን የሚመለከት ነዉ፡፡
ከላይ በተመለከቱት ሁለት አዲስ የጊዜ ንድፈ ሃሳቦች መሰረት እጅግ ረቅቀዉ የተሰሩት የአሰራር መሳሪያዎች ሁለት ናቸዉ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ እጅግ በጣም ረቅቆ የተሰራዉ የአሰራር ማሰሪያ ጳጉሜ 6 ነዉ፡፡ ምክንያቱም ጳጉሜ 6፡-ከሰባቱም ተግበራዊ የጊዜ መለኪያ አሃዶች በመትረፍ በየሦሥት ምድብ አራት አመት ማብቂያ ላይ በ12 ሰዓት ቀን እና 12 ሰዓት ለሊተ በእጅ ሰዓት እና በ24 ሰዓት እለት መደብ በኢትዮጵያ ቀን መቁጠሪያ ላይ የሚመዘገብ የሰሜንና ደቡብ ሰፊ ሞቃት ምድር እለት ማለት ሲሆን፤ በሁለተኛ ደራጃ እጅግ ረቅቆ የተሰራዉ የአሰራር መሳሪያ ሰብቴምበር 11 ነዉ፡፡ ምክንያቱም ሰብቴምበር 11 ከሰባቱም ተግበራዊ የጊዜ መለኪያ አሃዶች በመትረፍ በየሦሥት ምድብ አራት አመት ማብቂያ ላይ በረጅም ወይም አጭር ሰዓት ቀን እና አጭር ወይም ረጅም ሰዓት ለሊት በእጅ ሰዓት እና በ24 ሰዓት እለት መደብ በግሪጎሪያን ቀን መቁጠሪያ ላይ የሚመዘገብ የሰሜንና ደቡብ ጠባብ ቀዝቃዛ ምድር እለት ማለት ነው፡፡
እንዲሁም አሁን ያለንበት የተሳትፎ ዘመን አለም አቀፋዊ (ግሎባላዜሽን) ይባላል፡፡ በመሆኑም ከላይ በተመለከቱት ሁለት አዲስ የጊዜ ንድፈ ሃሳቦች መሰረት አለም አቀፍ (ግሎባላይዜሽን) ማለት የሰሜንና ደቡብ ሰፊ ሞቃት ምድር ወይም የሰፊ ሞቃት ምድረ ሰማይ (ጳጉሜ 6) ከሰሜንና ደቡብ ጠባብ ቀዝቃዛ ምድር ወይም የጠባብ ቀዝቃዛ ምድረ ሰማይ (ሰብቴምበር 11) ፍፁም የተለየ ማለት መሆኑን ከሚከተለዉ የምድር ምሥል 1.1 በቀላሉ ማየት እጅግ ጠቃሚ ነዉ፡፡
ከላይ ምስል 1.1 የምንረዳዉ አንድ ቦታ ላይ ሁለት እለት እና አመት በፍፁም ሊከሰት አለመቻሉን ነዉ፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ ቀን መቁጠሪያ ላይ ጳጉሜ 6 እና ሰብቴምበር 11 የሚመዘገቡት እና ሊመዘገቡ የቻሉበት ምክንያት ምንድን ነዉ? ጳጉሜ 6 እና ሰብጤምበር 11 በኢትዮጵያ ቀን መቁጠሪያ ላይ የሚመዘገቡት፤ የመጀመሪያዉ የሞቃት ምድር አሰራር መሳሪያ በመሆኑ ሲሆን፤ የሁለተኛዉ የቀዝቃዛ ምድር አሰራር መሳሪያ ቢሆንም አዚህ ሞቃት ምድር ላይ የምንኖር ሰዎች የእነርሱን ወር እለት ሥም እና ቁጥር እንድናዉቅ ሲባል ነዉ፡፡ ሥለዚህ በተመሳሳይ ሁኔታ በቀዝቃዛ ምድር የግሪጎሪያኑ ቀን መቁጠሪያ ላይ የኢትዮጵያ ቀን መቁጠሪያ ተመዝግቦ በቀዝቃዛ ምድር አገሮች ማሰራጨት አስገዳጅ የሚሆነዉ እነርሱም የሞቃት ምድር ወር እለት ማወቅ ስላለባቸዉ ነዉ፡፡
ጳጉሜ 6 እና ሰብጤምበር 11 በኢትዮጵያ ቀን መቁጠሪያ ላይ መመዝገብ የቻሉበት ምክንያት ሁለቱም ለየብቻ የሚያገለግሉ የፀሃይ ቀን መቁጠሪያዎች በመሆናቸዉ ነዉ፡፡
የጳጉሜ 6 ሳምንትና ዓመተ ምህረት ከሰብቴምበር 11 ሳምንት እና ዓመተ ምህረት ይለያል
የጳጉሜ 6 ሳምንት እና ዓመተ ምህረት ከሰብቴምበር 11 ሳምንት እና ዓመተ ምህረት ይለያል ማለት የሰሜንና ደቡብ ሰፊ ሞቃት ምድር የሳምንት እለት ስም፤ ወር እለት ስምና ቁጥር እና አመተ ምህረት ቁጥር ከሰሜንና ደቡብ ጠባብ ቀዝቃዛ ምድር የሳምንት እለት ስም፤ወር እለት ስምና ቁጥር እና የአመተ ምህረት ቁጥር ፍፁም የተለዩ መሆናቸዉን የሚገልፅ ነዉ፡፡ በመሆኑም የሁለት ወሮች እለት ስሞች ጳጉሜ 6 እና ሰብቴምበር 11 በኢትዮጵያ ቀን መቁጠሪያ ላይ በሦሥት ምድብ አራት አመት ማብቂያ ላይ ሳይለዋወጡ በመመዝገብ ላይ ናቸዉ፡፡ የሳምንት እለት ስሞች ግን በየ28 አመት እየዞሩ ይለዋወጣሉ፡፡ የእምርታ ዓመተ ምህረት ቁጥር በ4 አሃድ እየጨመረ ይመዘገባል፡፡ በዚህ ክፍል ጳጉሜ 6 እና ሰብቴምበር 11 የተመዘገቡበትንና የሚመዘገቡበትን ዓመተ ምህረቶች እና የሳምንት እለት ስም መረጃ በመተንተን ጳጉሜ 7 ማስረጃና መረጃ ሊቀርብለት የማይችል ዉሸት መሆኑን በተመለከተ በቂ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ነዉ፡፡
በመሆኑም ጳጉሜ 6 የሚመዘገብበት የሳምንት እለት ስም እና የእምርታ አመተ ምህረት የታወቁ፤እየታወቁ ያሉ እና ወደፊትም የሚታወቁ ናቸው፡፡ በቅድሚያ ጳጉሜ 6 እለት የሚውልበት አመት ምድብ ሦሥት ወይም የእምርታ አመት እለት ብዛት 366 ነው፡፡ በመሆኑም ከክርስቶስ ልደት ወዲህ የመጀመሪያው እና ሁለተኛዉ የእምርታ ዓመተ ምህረቶች . 3 እና 7 ነበሩ፡፡ በመሆኑም ጳጉሜ 6 እለት የዋለችባቸው 7ቱ ተከታታይ የባለ 366 እለት እምርታ አመተ ምህረቶች፡- 3፤7፤11፤15፤19፤23 እና 27 ነበሩ፡፡ እንዲሁም በየአራት አመት ጳጉሜ 6 የምትውልባቸው 7ቱ የሳምንት እለት ስሞች፡- እሁድእለት፤ አርብእለት፤ ረቡእለት፤ ሰኞእለት፤ ቅዳሜእለት፤ ሀሙስእለት እና ማክሰኞእለት ናቸው፡፡ ስለዚህ ከልደቱ ወዲህ ጳጉሜ 6 ለመጀመሪ ጊዜ ከሳምንት እለት ብዛት ጋር እኩል የሆነው እሁድእለት በ3 ዓ.ም.፤ አርብእለት በ7 ዓ.ም፤ረቡዕለት በ11 ዓ.ም፤ ሰኞእለት በ15 ዓ.ም፤ቅዳሜእለት በ19 ዓ.ም፤ ሐሙስእለት በ23ዓ.ም እና ማክሰኞእለት በ27 ዓ.ም ላይ በመዋልና በቀን መቁጠሪያ ላይ በመመዝገብ ነበር፡፡
እንዲሁም ጳጉሜ 6 የሚውልባቸው ዓ.ም ቁጥሮች የምናዉቀው በምድብ ሶስት አመተ ምህረት ወይም በጳጉሜ 6 መስመራዊ እኩልታ ነው፡፡ የምድብ ሶስት አመተ ምህረት መስመራዊ እኩልታ
ቀ=0.25+0.25ዓ_4 ነው፡፡
ፊደል ቀ ማለት ጳጉሜ 6 በእጅ ሰዓትና በቀን መቀጠሪያ ላይ የሚመዘገብበትን የምድብ 3 ባለ 366 እለት ዓመተ ምህረት ወይም የእምርታ አመት 7 ተከታታይ ቅድም ተከተልን የሚያሳይ ጥገኛ ተለዋዋጭ ማለት ነው፡፡ ከግርጌው ቁጥር 4 የያዘው ፊደል ዓ_4 ማለት በየ 4 አመት የሚከሰት የባለ 366 እለት ልዩ ዓመተ ምህረት መሁኑን የሚያሳይ ኢጥገኛ ተለዋዋጭ ቁጥር ማለት ነው፡፡ እንዲሁም መስመራዊ እኩልታው ሁለት የማይለዋወጡ እኩል ክፍልፋይ ቁጥሮች አሉት፡፡ የመጅመሪያው 0.25 ቁጥር በምድብ ሶሰት አመት በእጅ ሰዓት የማይመዘገበው የጳጉሜ 6 ብዛት 0.25 እለት ወይም 6 ሰዓት መሆኑን ሲገልፅ፤ የእኩለታው ግድለት ወይም ከምድብ ሶስት አመት ፊት የሚገኘው 0.25 አሃድ የሚናገረው የእምረታ አመቱ በ አንድ አሃድ ሲሮጥ፤ ቅደም ተከተሉ በ0.25 አሃድ እየጨመረ መሮጡን ያሳያል፡፡ በመሆኑም የምድብ ሶስት አመት ቅደም ተከተል ፊደል ቀ የምናውቀበት ዘዴ እጅግ ቀላል ነው፡፡ የፊደል ቀን ዋጋ በሂሳብ ስሌት በማግኘት ነው፡፡ ስለዚህ የ ቀ ዋጋ ማለት በምድብ አመት ያልተመዘገበው 0.25 እለት ሲደመር፤ የእኩለታው ግድለት 0.25 ሲባዛ በምድብ ሶስት የባለ 366 እለት ዓመተ ምህረት. ቁጥር፡፡ ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት ወዲህ የመጀመሪያው የባለ 366 እለት እምርታ ዓ.ም ቁጥር 3 ነበረ፡፡ በመሆኑም የመጀመሪያው ባለ 366 እለት ዓ.ም መሁኑን የሚያሳይ ኢጥገኛ ተለዋዋጭ ቁጥር ዋጋ ዓ_4=3 ነው፡፡ ይህን 3 ቁጥር በእኩልታው ፊደል ተክተን ሂሳቡ ሲሰላ የተገኘው ጥንድ ቁጥር 1 ነው፡፡
አስረጅ ቀ=0.25+0.25(3)
ቀ=0.25+0.75
ቀ=1
ትርጉሙም ጳጉሜ 6 ለመጀመሪያ ጊዜ እሁድእለት ላይ የዋለው በ 3 ዓ.ም ላይ ነበር ማለት ነዉ፡፡ ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት ወዲህ ሁለተኛው የባለ 366 እለት እምርታ ዓ.ም ቁጥር 7 ነበረ፡፡ በመሆኑም የሁለተኛው ባለ 366 እለት ዓ.ም መሁኑን የሚያሳይ ኢጥገኛ ተለዋዋጭ ቁጥር ዋጋ ዓ_4=7 ነው፡፡ ይህን 7 ቁጥር በኩልታው ፊደል ተክተን ሂሳቡ ሲሰላ የተገኘው ጥንድ ቁጥር 2 ነው፡፡
አስረጅ ቀ=0.25+0.25(7)
ቀ=0.25+1.75
ቀ=2
ትርጉሙም ሁለተኛው ጳጉሜ 6 ለመጀመሪያ ጊዜ አርብእለት ላይ የዋለው በ 7 ዓ.ም ላይ ነበር ማለት ነዉ ፡፡ ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት ወዲህ ሶስተኛው የባለ 366 እለት እምርታ ዓ.ም ቁጥር 11 ነበረ፡፡ በመሆኑም የሁለተኛው ባለ 366 እለት ዓ.ም መሁኑን የሚያሳይ ኢጥገኛ ተለዋዋጭ ቁጥር ዋጋ ዓ_4=11 ነው፡፡ ይህን 11 ቁጥር በኩልታው ፊደል ተክተን ሂሳቡ ሲሰላ የተገኘው ጥንድ ቁጥር 3 ነው፡፡ ትርጉሙም ሶስተኛው ጳጉሜ 6 ለመጀመሪያ ጊዜ እሮብእለተ ላይ የዋለው በ 11 ዓ.ም ነበር፡፡
ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት ወዲህ 500ኛዉ የባለ 366 እለት እምርታ ዓ.ም ቁጥር 1999 ነበረ፡፡ በመሆኑም የ500ኛው ባለ 366 እለት ዓ.ም የሚያሳይ ኢጥገኛ ተለዋዋጭ ቁጥር ዋጋ ዓ_4=1999 ነው፡፡ ይህን 1999 ቁጥር በኩልታው ፊደል ተክተን ሂሳቡ ሲሰላ የተገኘው ጥንድ ቁጥር 500 ነው፡፡ ትርጉሙም 500ኛው ጳጉሜ 6 ጊዜ ማክሰኞእለተ ላይ የዋለው በ 1999 ዓ.ም ላይ ነበር ማለት ነዉ፡፡
ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት ወዲህ 600ኛዉ የባለ 366 እለት እምርታ አመት የሚዉልበት ዓ.ም ቁጥር 2399 ነዉ፡፡ በመሆኑም የ600ኛው ባለ 366 እለት ዓ.ም መሁኑን የሚያሳይ ኢጥገኛ ተለዋዋጭ ቁጥር ዋጋ ዓ_4=2399 ነው፡፡ ይህን 2399 ቁጥር በኩልታው ፊደል ተክተን ሂሳቡ ሲሰላ የተገኘው ጥንድ ቁጥር 600 ነው፡፡ ትርጉሙም 600ኛው ጳጉሜ 6፤ አርብእለት ላይ ዉሎ የሚመዘገበዉ በ2399 ዓ.ም ላይ ነዉ፡፡ ሰብቴምበር 11፤ ፍራይዴ ላይ ዉሎ የሚመዘገበዉ በ2407 ዓ.ም ላይ ነዉ፡፡
ከ494ኛ እስከ 500ኛ ዙር ድረስ ከ1975 እስከ 1999 ዓ.ም ድረስ የነበሩት የጳጉሜ 6 እለቶች ዉለዉ የተመዘገቡት 7 የሳምንት እለት ሥሞች ከእሁድእለት እሰከ ማክሰኞእለት ነበረ ማለት ነዉ፡፡
599ኛ 2395 ዓ.ም ጳጉሜ 6 ተመዝግቦ የሚዉልበት የሳምንት እለት ሥም አሁድእለት ነዉ፡፡
600ኛ 2399 ዓ.ም ጳጉሜ 6 ተመዝግቦ የሚዉልበት የሳምንት እለት ሥም አርብእለት ነዉ፡፡
601ኛ 2403 ዓ.ም ጳጉሜ 6 ተመዝግቦ የሚዉልበት የሳምንት እለት ሥም ረቡዕለት ነዉ፡፡
602ኛ 2407 ዓ.ም ጳጉሜ 6 ተመዝግቦ የሚዉልበት የሳምንት እለት ሥም ሰኞእለት ነዉ፡፡
603ኛ 2411 ዓ.ም ጳጉሜ 6 ተመዝግቦ የሚዉልበት የሳምንት እለት ሥም ቅዳሜእለት ነዉ፡፡
604ኛ 2415 ዓ.ም ጳጉሜ 6 ተመዝግቦ የሚዉልበት የሳምንት እለት ሥም ሐሙስዕለት ነዉ፡፡
605ኛ 2419 ዓ.ም ጳጉሜ 6 ተመዝግቦ የሚዉልበት የሳምንት እለት ሥም ማክሰኞእለት ነዉ፡፡
ማጠቃለያ ፡
ጳጉሜ 6 የተመዘገበበት እና የሚመዘገብበት አመተ ምህረት እና የሳምንት እለት ስም የሚገኙት በኢትዮጵያ ቀን መቁጠሪያ ላይ ሲሆን፤ ሰብቴምበር 11 የተመዘገበበት እና የሚመዘገብበት አመት ምህረት እና የሳምንት እለት ስም የሚገኙት በግሪጎሪያን ቀን መቁጠሪያ ላይ ነው፡፡ሆኖም ግን ሁለቱም የፀሃይ ቀን መቁጠሪያ ስለሆኑ በኢትዮጵያ ቀን መቁጠሪያ ሰንጠረዥ ላይ በየአመቱ በመውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ለአብነት በቅርብ ያለፈዉ አርብእለት; ጳጉሜ 6፤2007 ዓ.ም ከፍራይዴይ ሰብቴምበር 11፡ 2015 ዓ.ም ፍፁም የተለየ ነዉ፡፡ እዚህ ኢትዮጵያ ዉሥጥ ብቻ ተሸሽጎ የሚገኘዉን ቀን መቁጠሪያ ከቅኝ ገዥ መስፋፋት በፊት ወደነበረበት አጠቃላይ የሰፊ ሞቃት ምድር መልሶ ሥራ ላይ ማዋል የአሁኑ አለምአቀፋዊ ተሳትፎ ዘመን አሰገዳጅ መሆኑን መገንዘብ ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ የማድረግ አመራር በኛ የኢተዮጵያዉ አፍሪካ ህዳሴ በዋናነት እና በመላዉ የአለም ህዝብ እጅ ላይ በመዉደቁ ጭምር ነዉ፡፡
We are in the process of making new worlds. The Tropics rotates and revolves faster than the Temperates. So that there are two technologies of time: Ethiopian calendar and Gregorian calendar. I used 68 years data to discover the truths of new worlds.
Tuesday, 12 April 2016
How one who unable to think is able to teach mathematics?
How one who unable to think is able to teach mathematics?
How one who unable to think is able to teach mathematics?
How one who unable to think is able to teach mathematics?
How one who unable to think is able to teach mathematics?
How one who unable to think is able to teach mathematics?
How one who unable to think is able to teach mathematics?
How one who unable to think is able to teach mathematics?
Subscribe to:
Posts (Atom)