የምድር 6 ሰቅዎች/ዞኖች
ሰቅ ማለት ዞን (zone) ማለት ነዉ ሲል በኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ አቻ ፍች ተሰጥቶታል፡፡ በመሆኑም ሰቅ ማለት ከምድረ ልክ (geography) 6 ሰቅዎች ውስጥ አነዱ ረጅም ወይም አጭር ልከ ሙቀት እና የፀሀይ ስርጭት የሚታይበት ምድር ማለት ነው፡፡ የምድር 6 ሰቅዎች መፈጠር ምክንያት የእንቁላል ቅርጽ ያላት ምድር ከፀሀይ ጋር ባላት የተፈጥሮ ቁርኝት ነው፡፡ ከሰሜን አውታር ተነስተን ወደ ደቡብ አውታር ስንወርድ 6 የተፈጥሮ ሰቆች መኖራቸውን ከምሥል 1.3 እንመለከታለን፡፡ በመሆኑም ሰቅ 1 የሰሜን በረዶ፤ ሰቅ 2 የሰሜን ጠባብ ቀዝቃዛ፤ ሰቅ 3 የሰሜን ሰፊ ሞቃት እና ሰቅ 4 የደቡብ ሰፊ ሞቃት፤ ሰቅ 5 የደቡብ ጠባብ ቀዝቃዛና ሰቅ 6 የደቡብ በረዶ ናቸው፡፡
የምድር ልከ ሙቀትንና የፀሀይ ዘዌ በተለያየ የምድር ቦታ ላይ የተለያዩ መሆናቸውን በመመልከት ምድርን ለመጀመሪያ ጊዜ በሰቅ(በዞን) ስርአት 5 ቦታ ብቻ በገዳሚ መስመሮች (lines of latitude) የከፈለው ሰው በ5ኛው መቶ ቅድመ ክርስቶስ ይኖር የነበረው ፓርሜኒደስ የተሰኘው የግሪክ ፈላስፋ ነው፡፡
የምድር 6 የተፈጥሮ ሰቅዎችን 5 ብቻ አድርጎ የበየነው የሰሜን እና ደቡብ ሰፊ ሞቃት 2 ሰቅዎችን እንደ አነድ ሰቅ በመቁጠር ነበር (a torrid zone between the Tropic of Cancer (about 23.5° N) and the Tropic of Capricorn (about 23.5° S) ፡፡ በመሆኑም እርሱ እንደ አንድ ሰቅ አድርጎ በመውሰዱ ምክንያት የሞቃት ምድር እሰካሁን ድርስ አለመገኘቱን (the Undiscovered Tropics) ያሳያል፡፡ ነገር ግን በምሥል 1.3 የተመለከተችውን ምድር ወገቧ ላይ ብናጥፋት ሰቅ 1 በሰቅ 6 ላይ፤ ሰቅ 2 በሰቅ 5 ላይ እና ሰቅ 3 በሰቅ 4 ላይ ያርፋል፡፡ ይህም ሰቅ 1 ከሰቅ 6፤ ሰቅ 2 ከሰቅ 5 እና ሰቅ 3 ከሰቅ 4 ምስስለት ቅልብሽ (symmetrical fold ) መሆናቸውን ያሳያል፡፡ በመሆኑም አሁን በምንገኝበት የኢትዮጵያ ህዳሴ ዘመን ግን ሰቅ 3 እና ሰቅ 4 እንደ አነድ ሰቅ አድረገን መውሰድ በፍጹም የማንችለው በተፈጥሮና ሳይነስ አሰገዳጅነት ምክንያት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ህዳሴ ማለት ጥንታዊ የግሪክ ፍልስፍናን፤ የአውሮጳ ህዳሴን ፍልስፍና ቴክኖሎጂ መልሰን በማግኘት እና እንዲሁም የኛን አዲስ ፍልስፍና በመጨመር የአሰራር መሳሪያ በመስራት እና በመተግበር አዲሲቷን አለም የመፍጠር ሥራን የሚያጠቃልል በመሆኑ ነው፡፡
No comments:
Post a Comment