Sunday, 31 May 2015

የሞቃቱ ምድር እና የቀዝቃዛው ምድር እንዴት ቢሾሩና ቢዞሩ ነው? ሹረታቸውን እና ዙረታቸውን እኩል በየ24 ሰዓትና በየ365.25 እለት የሚፈጽሙት?

"አንድ እለት ማለት የምደር አንድ ጊዜ ሹረት መሆን በሳይንሰ ያለቀለት ጉዳይ ነው፡፡ ሥለዚህ በዚህ ዙሪያ ማን ምን ብሎ ይጠይቃል"
በሚል ያቀረቡት መከራከሪያ ሐሳብ ምንም እንኪን የምድር ሹረትንና ዙረትን ማወቅዎንና ማመንዎን ባይገልጽም የተጠቃለለ ብያኔ ነው፡፡ ምድር በራሷ ዛቢያ የምትሾረው በየ 24 ሠዓት ነው የሚል የተጠቃለለ ብያኔ ለምድር ወገብ ብቻ በመቆሙ ነው፡፡ ነገር ግን የምድራችን ቅርፅ ምላላ ክብ ሲሆን የምቃቱ ምድር ዙሪያ ረጅም ወይም ሰፊ ሲሆን፣ የቀዝቀዛው ዙሪያ አጭር ወይም ጠባብ ነው፡፡ ሥለዚህ ሁለት አዲስ ያላለቀላቸው ጥያቄዎች አሉ፡፡ ጥያቄዎቹ ረጅም ዙሪያ ያለው ሞቃት ምድር እና አጭር ዙሪያ ያለው ቀዝቃዛ ምድር እንዴት ቢሾሩና ቦዞሩ ነው አንድ ሙሉ ሹርትን በየ 24 ሠዓት እና ዙረትን በየ365.25 እለት እኩል የሚጨርሱት ? የሚሉ ነቸው፡፡

ሀ. የሞቃቱ ምድር እና የቀዝቃዛው ምድር እንዴት ቢሾሩ ነው? ሹረታቸውን እኩል በየ 24 ሠዓት የሚፈጽሙት?

የምድራችን ቅርፅ ምላላ ክብ ሲሆን የምቃቱ ምድር ዙሪያ ረጅም ወይም ሰፊ ሲሆን፣ የቀዝቀዛው ዙሪያ አጭር ወይም ጠባብ ነው፡፡ ሥለዚህ አዲሱ ጥያቄ ረጅም ዙሪያ ያለው ሞቃት ምድር እና አጭር ዙሪያ ያለው ቀዝቃዛ ምድር እንዴት ቢሾሩ ነው አንድ ሙሉ ሹርት እኩል በየ 24 ሠዓት የሚጨርሱት የሚል ነው ፡፡ መልሱም እጅግ በጣም ቀላል ነው፡፡ ረጅም ዙሪያ ያለው የሞቃቱ ምድር እና አጭር ዙሪያ ያለው የቀዝቃዛው ምድር ሹረታቸውን እኩል በየ 24 ሠዓት የሚፈጽሙት፣ የሞቃቱ ምድር እየፈጠነ እና ቀዝቃዛው ምድር እየተንቀረፈ በመሾር ነው፡፡

ለ. የሞቃቱ ምድር እና የቀዝቃዛው ምድር እንዴት ቢዞሩ ነው? ዙሩን እኩል የሚጨርሱት?

የሞቃት ምድር እና የቀዝቃዛ ምድር ዙረታቸውን እኩል በየ 365.25 እለት የሚጨርሱት፣ ሞቃቱ ምድር እየፈጠነ እና ቀዝቃዛው ምድር እየተንቀረፈፈ በመዞር ነው፡፡ በመሆኑም በሰሜንና ደቡብ ሞቃቱ ምድር የሚከሰቱት አራት፤ አራት መካከለኛ ተቃራኒ ወቅቶች እና እጅግ የተቀራረበ አጭር የቀንና ለሊት ልዩነት፤ በሰሜንና ደቡብ ቀዝቃዛ ምድር ከሚከሰቱት አራት፤ አራት ከፍተኛ ተቃራኒ ወቅቶች እና እጅግ ከተራራቁት የቀንና ለሊት ልዩነት የተለዩ ናቸው፡፡ በመሆኑም ሁለት አዲስ የጊዜ ንድፈ ሀሳብ መስራት ይቻላል፡፡ አንደኛው አዲስ የጊዜ ንድፈ ሀሳብ፡ አጭር የቀንና ለሊት ልዩነት እና መካከለኛ ወቅት ማለት የሞቃት ምድር ፈጣን ሹረት እና ዙረትን የሚመለከት ንድፈ ሃሳብ ሲሆን፤ ሁለተኛው አዲስ የጊዜ ንድፈ ሀሳብ ማለት እጅግ የተራራቀ የቀንና ለሊት ልዩነት እና ከፍተኛ ወቅቶች ማለት የቀዝቃዛ ምድር ቀርፋፋ ሹረት እና ዙረት መኖሩን የሚመለከት ንድፈ ሃሳብ ነው፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያ ቀን መቁጠሪያ የተሰራው የሞቃት ምድር ጊዜ ንድፈ ሃሳብ መኖሩን መሰረት አድርጎ ሲሆን፡የግሪጎሪያን ቀን መቁጠሪያ የተሰራው ግን የቀዝቃዛውን ምድር ጊዜ ንድፈ ሃሳብ መኖርን መሰረት አድርጎ መሆኑን መገንዘብ ይኖርብናል፡፡

No comments:

Post a Comment