We are in the process of making new worlds. The Tropics rotates and revolves faster than the Temperates. So that there are two technologies of time: Ethiopian calendar and Gregorian calendar. I used 68 years data to discover the truths of new worlds.
Sunday, 10 May 2015
የኢትዮጵያን ቀን መቁጠሪያ ተግባራዊ ጥቅም አውርደን ተቀምን ማለት የሚቻለው መቼ ነው?
"አንፃራዊ ጊዜን /ዘመንን፣ እንደነ አልበርት እና ስቴፊንግ ሆውኪንግ ያሉ የሳይንስ ጭንቅሌዎች በ20ኛው መቶ ክ/ዘመን ከልደት ወዲህ ሊደርሱባት የቻሉትን የጊዜ ዘመን ፍቺ ከጥንት ጀምሮ ይዞ፣ ተግባራዊ ጥቅም ላይ በሚውልበት አያያዝ አውርዶ ሲጠቀምበት የኖረ የዘመንና የዓለም ሐሳብ ነው"
ከላይ በተገለጸው መከራከሪያ ሀሳብ መሰረት የአንፃራዊ ጊዜን ትርጉም የሚያወቁ ከሆነ፤የኢትዮጵያን ቀን መቁጠሪያ ለምን ጥንታዊ ብቻ አድርገዉ ደመደሙ የሚለውን ጥያቄ መመለስ አለብዎት፡፡ጥንት ማለት ዛሬንና ነገን ማየት የማይችል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ የአንፃራዊ ጊዜን ትርጉም ሳይረዱ ስለጊዜ መናገር ኢሳይንሳዊና ኢተፈጠሮዋዊ ነው፡፡ ስለዚህ ከላይ ቀጥለው የገለጽት … ተግባራዊ ጥቅም ላይ በሚውልበት አያያዝ አውርዶ ሲጠቀምበት የኖረ የዘመንና የዓለም ሐሳብ ነው የሚለው ሐሰት ቢሆንም፤ የሚከተለውን አዲስ ጥያቄ በመፍጠሩ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ቀን መቁጠሪያ ተግባራዊ ጥቅም አውርደን ተቀምን ማለት የሚቻለው መቼ ነው?
የኢትዮጵያን ቀን መቁጠሪያ ተግባራዊ ጥቅም ላይ ልናውል የምንችለው በዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ ከማንኛውም ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ እሴት የተዘለለችውን ጳጉሜ ማግኘት ብቻ ሳይሆን የግሪጎሪያኑን ቀን መቁጠሪያ ኢተፈጥሮዊና ኢሳይንሳዊ ጥቅም በማስቀረት በሞቃት ምድር ውስጥ የሚከሰቱት የተፈጥሮ ወቅቶች፣ አጭር ቀንና ሌሊት ሠዓት ልዩነት እና ማናቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ሃይማኖታዊ ሥራዎች ሲመዘገቡበት ብቻ ነው፡፡
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment